መስጊድ እና በኅብረተሰቡ ውስጥ ያለው ሚና

በባልታዛር እና አብደናጎ

ክፍል አንድ 

የእስልምና ንፅረተ-ሕይወት፡ በሕይወትና በሃይማኖት ላይ

በሕይወት እና በሃይማኖት መካከል ስላለው ግንኙነት እስላማዊው ማኅበረሰብ የሚያስበው ሌሎች ኅብረተሰቦች ከሚያስቡት በጣም የተለየና ከስረ-መሠረቱ ጀምሮ። እስላማዊ ባልሆኑ ኅብረተሰቦች መካከል ሕይወትን በተመለከተ ከ“ሃይማኖት” ያለፈ ብዙ ነገር ይካተታል። በተጨማሪም የምንከተለውን ሃይማኖት የመምረጥ ነፃነት በሌሎች የሚከበርና ሕግም የሚደግፈው ግላዊ ጉዳይ ነው።

ሕይወትና ሃይማኖት በእስልምና

“ምርጫ” የሚባለው ሐሳብ በራሱ በእስልምና የተወገዘ ከመሆኑ ባሻገር እንደ ኢ-እስላማዊ (ፀረ-ኢስላም) ፅንሰ-ሐሳብ ተደርጎ ይቆጠራል። የምርጫ ነፃነት የሚባል ነገር ካለመኖሩም ባሻገር ሃይማኖት የግል እና ግላዊ ጉዳይ አይደለም።

በእስልምና ውስጥ ሕይወትና ሃይማኖት በጥልቅ የተቆራኙና የማይነጣጠሉ ናቸው። አንድ ሙስሊም ሃይማኖቱን ለሌላ እምነት ሲል ቢተው በእስላማዊው ሕግ መሠረት ከፍተኛና በሞት የሚያስቀጣ የክህደት ወንጀል ይሆናል።

“በሃይማኖት ማስገደድ የለም” የሚለው የሃይማኖት ነፃነት በተነሳ ቁጥር በሙስሊሞች የሚጠቀሰው ጥቅስ እንደ አስፈላጊነቱ ይጠመዘዝና ይተረጎማል።  የሚገኘውም በሁለተኛው ምዕራፍ ቁጥር 256 ላይ ነው። ይህ እና እንደዚህ ያሉት በጥቂቱ ምርጫን የመለዋወጥን ጉዳይ የሚያወሱ አስቀድሞ በመሐመድ ስብከቶች ውስጥ የተካተቱ ጥቅሶች ተወግደው እስላማዊው ሕግ አውጪና የተከበረው የቁርኣን ተርጓሚ ባለሥልጣን ባስቀመጣቸው ቀጣይ መገለጦች ተተክተዋል።

በሃይማኖት ምርጫ ላይ ማስገደድ ከሌለና ይህም በእርግጥ እውነት ከሆነ፤ የሳውዲ የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ ማንኛውም በሳውዲ አረቢያ ውስጥ የሚገኝ ሙስሊም ሃይማኖቱን ከለወጠ በሞት እንዲቀጣ የሚደነግገው ለምንድነው? የአፍጋኒስታን ዜጋ የሆነውና ወደ ክርስትና የመጣው አብዱል ራህማን በእስር እየማቀቀ የሞት ቅጣት የሚጠባበቀው ለምንድነው? መህዲ ዲባጅ እምነቱን ወደ ክርስትና በመለወጡ ምክንያት በኢራን መንግሥት ወኪሎች የተገደለው ለምንድነው? የኢራን ባለሥልጣናት ሃይማኖታቸውን ወደ ባሀኢ የለወጡትን ዜጎቻቸውን የሚያሳድዷቸው ለምንድን ነው ?

በየትኛውም እስላማዊ ዓለም ውስጥ አንድ ሙስሊም በግልፅ ሃይማኖቱን መለወጡን ወይም እስልምናን መተዉን ያስታወቀ እንደ ሆነ የመገለል፣ በሕጋዊ አካል የመሰቃየት፣ የመታሰርና አለፍ ሲልም የሞት ከባድ ቅጣቶች ይጠብቁታል።

አንድ ሰው እንዲያው ማንንም ለማስከፋት ባልታለመ ሁኔታ እንደ “የእስልምናው ነቢይ መሐመድ የተቀደሰ አልነበረም” ወይም “እስልምና ብቸኛው ሃይማኖት አይደለም” ያሉ ንግግሮችን ቢናገር በየትኛውም እስላማዊ ዓለም ውስጥ አምላክን እንደ ሰደበና ከሀዲ እንደሆነ ይቆጠራል። ለምሳሌ እንዲህ ያለው ንግግር፣ በፓኪስታን የወንጀለኛ መቅጫ ሕግ 295 አንቀጾች ሀ፣ ለ እና መ መሠረት ከአሥር ዓመት እስከ ዕድሜ ልክ እስራት እንዲሁም የሞት ቅጣት ያስቀጣል።

የሚከተሉት እና እንደዚሁ ያሉ የቁርአን ጥቅሶች “በሃይማኖት ማስገደድ የለም” የሚለውን በተደጋጋሚ የሚነገር ጥቅስ ሽረውታል፤

የተከበሩትም ወሮች ባለቁ ጊዜ አጋሪዎቹን በአገኛችሁባቸው ስፍራ ግደሉዋቸው። ያዙዋቸውም፣ ክበቡዋቸውም፣ ለእነሱም (መጠባበቅ) በየመንገዱ ተቀመጡ። ቢፀፀቱም፣ ሶላትንም በደንቡ ቢሰግዱ፣ ግዴታ ምፅዋትንም ቢሰጡ መንገዳቸውን ልቀቁላቸው። አላህ መሓሪ አዛኝ ነውና። ከአጋሪዎችም አንዱ ጥገኝነትን ቢጠይቅ የአላህን ቃል ይሰማ ዘንድ አስጠጋው። ከዚያም ወደ መጠበቂያው ስፍራ አድርሰው። ይህ እነሱ የማያውቁ ሕዝቦች በመኾናቸው ነው። ለአጋሪዎቹ አላህ ዘንድና እመልክተኛው ዘንድ ቃል ኪዳን እንዴት ይኖራቸዋል? እነዚያ በተከበረው መስጊድ ዘንድ ቃል ኪዳን የተጋባችኋቸው ብቻ ሲቀሩ። (እነዚህ) በቃል ኪዳናቸው ለእናንተ ቀጥ እስካሉላችሁ ድረስ ለነርሱም ቀጥ በሉላቸው። አላህ ጥንቁቆችን ይወዳልና። በእናንተ ላይ ቢያይሉም በእናንተ ውስጥ ዝምድናንና ቃል ኪዳንን የማይጠብቁ ሲኾኑ እንዴት? (ቃል ኪዳን ይኖራቸዋል)። በአፎቻቸው ያስወድዷችኋል። ልቦቻቸውም እንቢ ይላሉ። አብዛኞቻቸውም አመፀኞች ናቸው።

በአላህ አንቀፆች ጥቂትን ዋጋ ገዙ። ከመንገዱም አገዱ። እነርሱ ይሠሩት የነበሩት ሥራ ከፋ! በምእምን ነገር ዝምድናንም ኪዳንንም አይጠብቁም፤ እነዚያም እነሱ ወሰን አላፊዎች ናቸው። ቢፀፀቱም፣ ሶላትንም ቢሰግዱ፣ ዘካንም ቢሰጡ የሃይማኖት ወንድሞቻችሁ ናቸው። ለሚያውቁ ሕዝቦችም አንቀፆችን እናብራራለን። (ቁርአን 9፡5፣11)

ለነዚያ ለካዱት በላቸው፡- ቢከለከሉ ለእነሱ በእርግጥ ያለፈውን (ሥራ) ምሕረት ይደረግላቸዋል። (ወደ መጋደል) ቢመለሱም (እናጠፋቸዋለን)። የቀድሞዎቹ ሕዝቦች ልማድ በእርግጥ አልፋለችና። ሁከትም እስከማትገኝ ሃይማኖትም ሁሉ ለአላህ ብቻ እስከሚኾን ድረስ ተጋደሏቸው። ቢከለከሉም አላህ የሚሠሩትን ሁሉ ተመልካች ነው። (ከእምነት) ቢዞሩም አላህ ረዳታችሁ መኾኑን ዕወቁ። (ቁርአን 8፡38-39)

በተጨማሪም መላው ምሑራን በአንድ ድምፅ በተስማሙበት ሁኔታ እስላማዊው ሕግ አውጪና ሸሪዓ “በሃይማኖት ማስገደድ የለም” የሚለውን ጥቅስ የሚፈቱት አረቦች፣ አይሁዳውያን ክርስቲያኖች፣ ሃይማኖት የለሾች እንዲሁም አረመኔዎች ወደ እስልምና የመምጣት ነፃነት እንዳላቸው እንጂ ከእስልምና ወደ ሌላ መቀየር እንደማይችሉ እንደሚናገር አድርገው ነው። ነፃነት መስጠቱ ነው ከተባለ ደግሞ የሰጠው የአንድ አቅጣጫ ነፃነት ብቻ ነው። በአሁኑ ጊዜ በምዕራቡ ዓለም የሚገኙ የእስልምና መሪዎች የትኛውም ሙስሊም ሃይማኖቱን ከእስልምና ወደ ሌላ ቢቀይር እንደማይገደል አውጀዋል፤ ነገር ግን ይህንን ያስቀመጡት ለመገናኛ ብዙሃን እወጃ ሲሉ ብቻ ይሆናል። ይህ ነገር ትክክል ከሆነ ተገቢው ፋትዋ (በእስላማዊው ሸሪዓ የወጡና በቁርአን እና በሐዲስ ማጣቀሻዎች ሙሉ በሙሉ የተደገፉ ግልፅ ሕግጋት ናቸው) እንዲወጣ አድርገው እንደ ኦርጋናይዜሽን ኦፍ ኢስላሚክ ኮንፍረንስ፣ ዘ ሙስሊም ወርልድ ሊግ፣ ዘ ዩኒየን ኦፍ ኢስላሚክ ኡላማ ወይም በግብጽ ካይሮ እንዳለው አል አሕዛር ዩኒቨርሲቲ ያሉ ሌሎችም ስማቸውን ለመጥራት የሚያዳግት ተቋማቶቻቸውም እንዲቀበሉ ለምን አያደርጉም?

ማብራሪያዎች

እባካችሁ የሚከተሉትን ሁለት ማብራሪያዎች በጥንቃቄ ተመልከቷቸው። ምስል 1 እስላማዊ ያልሆነውን ሁኔታ ያብራራል፤ ሃይማኖት በሕይወት ውስጥ የሚጫወተው የተወሰነ ሚና ነው።

ምስል 1፦ ሕይወት እና ሃይማኖት እስላማዊ ባልሆነው ንፅረተ-ዓለም ውስጥ

የመጀመሪያው ክብ ሕይወት ተብሎ ሲጠራ ሃይማኖት የዚያ ሕይወት ጥቂቱ አካል ሆኖ ይታያል። ይህም አንድ ሰው የቱንም ያህል ለእምነቱ ቀናዒ ቢሆን የት እና መቼ አምልኮ ማድረግ እንዳለበት፣ ግላዊ ፀሎቶቹን በምን ሰዓት ማድረስ እንዳለበት፣ ፊቱን ወደ የት መልሶ መፀለይ እንዳለበት፣ የሚመገበውን ምግብ፣ ከማን ጋር እንደሚወዳጅ ወ.ዘ.ተ በሙሉ ነፃነት የሚወስነው ራሱ ነው።

አሁን ደግሞ ምስል 2ን ተመልከቱና ከምስል 1 ጋር አነፃፅሩ። እስላማዊው አመለካከት መላው ክቡ በሃይማኖት የተሞላበት እና ለሕይወት ቅንጣት ቦታ የተሰጠበት ነው። በእስላማዊው ንፅረተ-ዓለም መሠረት ሃይማኖት ሁሉንም ነገር ይሆናል ማለት ነው። ከግላዊ የንፅሕና አጠባበቅ ደንቦች አንስቶ በማኅበረሰቡ ውስጥ የሚከናወኑ ዋና ዋና ጉዳዮችን ጨምሮ በሕይወት ውስጥ ያለው ነገር ሁሉ የሚገኘው ከሃይማኖት ነው።

ምስል 2፦ ሕይወትና ሃይማኖት በእስልምና ንፅረተ-ዓለም ውስጥ
 
የእስልምና ፍቺ

እስልምና ምዕራባውያን ቃሉን በሚያስቡበት መልኩ ሃይማኖት ብቻ ተደርጎ የሚቆጠር ወይም እምነት ብቻም አይደለም። ነገር ግን ሁሉን-አቀፍ ስልት ነው። በቀዳሚነት እና በዋነኛነት ማኅበራዊ-ፖለቲካዊ እና ማኅበራዊ-ሃይማኖታዊ ስርዓት ሲሆን በሃይማኖታዊ ቃላት የተሸፈነና የተጀቧቦነ ማኅበራዊ-ምጣኔ ሀብታዊ፣ ማኅበራዊ-ትምሕርታዊ፣ ሕግ አርቃቂ፣ ሕግ አውጪና ሕግ አስፈጻሚ ዘይቤ ነው። የተከታዮቹን እያንዳንዷን የሕይወት ክፍል፣ እርስ በርስ ያላቸውን ግንኙነት እንዲሁም ሙስሊም ካልሆኑ ሰዎች ጋር ያላቸውን ግንኙነት የሚቆጣጠር ነው።

የሙስሊሙን ማኅበረሰብ ሕይወት እና ሁሉንም የሕይወታቸውን ክፍል በመቆጣጠር ማዕከላዊውን ሚና የሚጫወተው ዋነኛ ተቋም መስጊድ ነው።

የአምልኮ ስፍራን በተመለከተ እስልምና እና ሌሎቹ ሃይማኖቶች (ለምሳሌ፦ ክርስቲያኖች፣ አይሁዶች፣ የሂንዱ እምነት ተከታዮች ወ.ዘ.ተ) የሚጠቀሙት ቃል ተመሳሳይ ቢሆንም እሳቤዎቹና ፍቺዎቹ በቀጥተኛና በተጨባጭ ሁኔታ የተለያዩ ናቸው። በሌላ አነጋገር የእስልምናን እሳቤዎች፣ መሠረተ-እምነቶች እና ተቋማት በሌሎቹ እምነቶች ውስጥ ከሚገኙት ጋር ማመሳሰል ወይም አንድ አድርጎ መመልከት አንችልም ደግሞም የለብንም፤ እንዲያ ማድረግ አጥፊ ስሕተት እና አደናጋሪ ይሆንብናል።

ሁለቱ ዋና ዋና ክፍሎች

እስልምና በአጠቃላይ በሁለት ዋና ዋና ክፍሎች ላይ የተመሠረተ ነው፦

  1. ቁርአን፦ መሐመድ ከአላህ በገብርኤል አማካይነት በ23 ዓመታት ጊዜ መካከል ጥቂት በጥቂት እንደወረደለት የሚነገረው መጽሐፍ ነው።
  2. ሱና፦  ከቁርአን እኩል ወይም ከቁርአን በበለጠ ሁኔታ ጠቃሚ እንደሆነ የሚታመን የመሐመድ ምሳሌዎች የተሰባሰቡበት መጽሐፍ ነው። መሐመድ በቃልና በተግባር ያስተማራቸውን ትምህርቶች እና እንዲደረጉ ያዘዛቸውን ማንኛቸውንም ነገሮች ያካትታል። ይህ ሱና ወይም የነብዩ መሐመድ የሕይወት ምሳሌ ለእስልምና ምትክ-የለሽ ነው። ሱና ካልተገለጠ በቀር በየትኛውም የእስልምና ልምምድ እና እምነት ላይ እርግጠኛ መሆን፣ እንዲሁም ቁርአንን መረዳት አይቻልም።

ለሙስሊሙ ማኅበረሰብ መሐመድ ከፍተኛውና በብዙ አክብሮት የሚመለከቱት አርአያቸው ስለ ሆነ እርሱን ሊመስሉና በቁርኣናዊ ደንቦች አማካይነት ሊታዘዙት ይገባቸዋል፦

“አንተም በታላቅ ጠባይ ላይ ነህ። ወደፊትም ታያለህ፤ ያያሉም። ዕብደት በማንኛችሁ እንዳልለ።” (ቁርአን 68.4)

“ነቢያችሁ (ሙሐመድ) አልተሳሳተም፤ አልጠመመምም። ከልብ ወለድም አይናገርም።እርሱ (ንግግሩ) የሚወርረድ ራእይ እንጅ ሌላ አይደለም። ኀይሎቹ ብርቱው (መልአክ) አስተማረው። የዕውቀት ባለቤት የኾነው (አስተማረው፤ በተፈጥሮ ቅርጹ ኾኖ በአየር ላይ) ተደላደለም። እርሱ በላይኛው አድማስ ኾኖ።” (ቁርአን 53.2-5)

“ለእናንተ አላህንና የመጨረሻውን ቀን የሚከጅል ለሆነ ሰው፣ አላህንም በብዙ ለሚያወሳ በአላህ መልዕክተኛ መልካም መከተል አልላችሁ።” (ቁርአን 33.21)

“መልክተኛውን የሚታዘዝ ሰው በእርግጥ አላህን ታዘዘ። ከትእዛዝም የሸሸ ሰው (አያሳስብህ)። በእነሱ ላይ ጠባቂ አድርገን አልላክንህምና።” (ቁርአን 4.80)

“እኛ መስካሪ አብሳሪና አስፈራሪም አድርገን በእርግጥ ላክንህ። በአላህ ልታምኑ፣ በመልክተኛውም (ልታምኑ)፣ ልትረዱትም፣ ልታከብሩትም፣ (አላህን) በጧትና ከቀትር በኋላ ልታወድሱትም (ላክነው)። እነዚያ ቃል ኪዳን የሚጋቡህ ቃል ኪዳን የሚጋቡት አላህን ብቻ ነው። የአላህ እጅ (ኀይሉ) ከእጆቻቸው በላይ ነው። ያፈረሰም ሰው የሚያፈርሰው በነፍሱ ላይ ብቻ ነው። በእርሱ ላይ አላህን ቃል ኪዳን የተጋባበትን የሞላም ሰው ታላቅ ምንዳን በእርግጥ ይሰጠዋል።” (ቁርአን 48.8-10)

“አላህ ከከተሞቹ ሰዎች (ሀብት) በመልክተኛው ላይ የመለሰው (ሀብት) ከእናንተ ውስጥ በሀብታሞቹ መካከል ተዘዋዋሪ እንዳይኾን። ለአላህና ለመልክተኛው፣ ለዝምድና ባለቤትም፣ አባት ለሌላቸው ልጆችም፣ ለድኾችም፣ ለመንገደኛም (የሚስሰጥ) ነው። መልክተኛውም የሰጣችሁን (ማንኛውንም) ነገር ያዙት። ከእርሱም የከለከላችሁን ነገር ተከልከሉ። አላህንም ፍሩ። አላህ ቅጣተ ብርቱ ነውና።” (ቁርአን 59.7)

ስለዚህ፤ ማንኛውንም ጉዳይ ከእስልምና አንፃር ስንመለከት ትክክለኛውን መልስ የምናገኘው በእነዚህ ባለ ሁለት ክፍል መሠረቶች ላይ በመመርኮዝ ባለስልጣኑ ያወጣቸውና በየመስጊዱ የተሰራጩ ሆነው ይገኛሉ።

የአዘጋጁ ማሳሰቢያ፡

የእስልምና እምነት ዋና ዋና መሰረታዊ ትዕዛዛት የሚመነጩትና የሚሰራጩት ከመስጊዶች ውስጥ ነው፡፡ የስልጣን መሠረታቸው ደግሞ ሁለቱ ማለትም ቁርአንና ሱናም እንደሆኑ የከዚህ በላዩ ጽሑፍ በግልፅነት ያስረዳል፡፡

እስልምና ተከታዮቹን በጥብቅ ቁጥጥር ስር ያደረገ ሃይማኖት መሆኑ የሚታወቅ ቢሆንም ከሃይማኖቱ እውነታ እንደምንረዳው ከሃይማኖትነት ያለፈ ስነ-ስልት ከመሆኑ የተነሳ ሙሉ ለሙሉ ሃይማኖት ብቻ ነው ለማለት ያስቸግራል፡፡

የሰው ልጅ ሁሉ መሰረታዊና ዘላለማዊ የሆነ እንዲሁም በፍፁም ችላ ሊለው የማይችለው ጥልቅ ጥያቄ አለው፡፡ አንድ በእግዚአብሔር ላይ የተመሰረተ ሃይማኖት ደግሞ የሰውን ልጅ ጥልቅ ጥያቄ በተመለከተ የሚሰጠው ትክክለኛ ምላሽ ሊኖረው ይገባል፡፡ ይህ ጥልቅ የሰዎች ልጆች ጥያቄ በቀጥታ የተያያዘው ከዘላለማዊ ነፍስ የመኖር እውነታ ጋር ነው፡፡ የዚህ ገፅ አዘጋጆች ዋና ሸክም ዘላለማዊዋና ክቡር የሆነችው የሙስሊሞች ነፍስ እውነተኛውን የነፍስ አዳኝ በማግኘት የዘላለም ሕይወት ጥልቅ ጥያቄዎቻቸው እንዲመለስላቸውና በአዳኙ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ ያለውን የሕይወት ትርጉምና ዓላማ እንዲያውቁ መርዳት ነው፡፡

ይህ ክቡር የሆነ ዓላማ እንዴት እውን ሊሆን ይችላል? ይህ እውን ሊሆን የሚችለው መጽሐፍ ቅዱስን በቅንነት በማንበብና የእግዚአብሔርን እውነት ለመፈለግ ልብን በማዘጋጀት፣ ኃጢአትን በእውነት በመናዘዝ ወደ እግዚአብሔር በእምነት ቀርቦ በክርስቶስ በኩል የኃጢአት ይቅርታን በመጠየቅ ነው፡፡ እግዚአብሔር ይርዳችሁ!

ወደ ማውጫው መመለሻ

ለእስልምና መልስ አማርኛ  ዋናው ገጽ